ሻደይ በጣም ያሸበረቀና የሚስብ የሴቶች በዓል ነው፡፡ የሻደይ ቃል የተወሰደው ከቅጠል ነው ይህንም ቅጠል ለዝግጅቱ በዓል ይጠቀሙታል በዓሉም በየአመቱ ነሃሴ 16-21 ይከበራል፡፡ በዓሉ ሃይማኖታዊም ታሪክ አለው በመሪያቸው አማካይነት ከሃይማኖታዊ ቦታ ከቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ይሰበሰባሉ በትንሳኤውም ይወጣሉ በአራቱም አቅጣጫ ያሉ ቡድኖች ይገናኛሉ የምስጋና ዘፈኖችን ከቤተክርስቲያን ካደረሱ ቡኋላ ወደ ሌሎች አለማዊ ቦታ ይሄዳሉ፡፡ የሴቶች በዓል የሆነ ታሪክ ነው በዓሉም የሚዘጋጀው በባህላዊ ቀለማት ባሸበረቁ ልብሶችን ለብሰው ይውላሉ፡፡ በዓሉ የባህላዊ አልባሳትን አይነቶችና የሴቶችን ባህላዊ ዘፈን ውድድር ለማየት ምቱ አጋጣሚን ይፈጥራል፡፡ ጫወታቸውን ሲጀምሩ በአቅራቢያቸው ባለ ቤተክርስቲያን በሰላምና በጤና ለዝግጅቱ ስለመድረሳቸው ከሻደይ ቅጠል ቆርጠው ወደ ቤተክርስቲያኑ ስጦታ ይጥላሉ ቀጥሎም ለቀጣይ አመት በሰላምና በጤና እንዲያደርሳቸውይፀልያሉ ምስጋናም ያቀርባሉ ከዚያም ወደ ተከበረ ትልቅ ሰው ወይም መሪ በመሄድ ባህላዊ ዘፈኖችን ያቀርባሉ እናም ስጦታም ይቀበላሉ፡፡
ሻደይ ነሽ አሉ ሻደይ ሻደይ ነሽ አሉ በያገሩ አሽከር አበባዬ . . . . . . . አሽከር አበባ አሽከር አበባዬ . . . . . . . አሽከር አበባ ሻደይ ነሽ አሉ ሻደይይህን እየተጫወቱ ቤተክርስቲያኑንም እያወደሱ ይጨፍራሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ቤተክርስቲያን የተገኙ የሃይማኖት አባት ወይም አቃቢት ወይም ማንኛውም ሌላ ሰው ይመርቋቸው፡፡ ‹‹ ተባረኩ፣ የከርሞ ሰው ይበላችሁ›› ብለው፡፡ በዚህ ጊዜ የሚሰጥ ነገር አይጠበቅም፡፡ በሹም ወይም በእድሜ ገፋ ካሉት ሽማግሌ ቤት አበባ ሲጥሉና ሲጫወቱ ግን የሚሰጥ ስጦታ ይኖራል፡፡ ከላይ ያየነውን ዜማ ከማለታቸው በፊትም እንዲህ እያሉ ከግቢው አጥር ላይ ሆነው ይዘፍናሉ
አስገባኝ በረኛ . . . . . . . .አስገባኝ ከልካይ . . . . አስገባኝ እመቤቴን ላይ . . . . . . . አስገባኝ ከልካይ . . . . . . . . . .አስገባኝ እመቤቴን ላይ . . . . . . .. አስገባኝ ከልካይ . . . . . . . . . አስገባኝይህን ከዘፈኑና ከተጫወቱ በኋላ ነው ከላይ ያያነውን የሚጫወቱት ወደ ሹም ወይም አንጋፋ የሃገር ሽማግሌ ቤት ሲገቡ፡፡ ከዚያም እንዱህ እያሉ ይዘፍናሉ፡-
ሻደይ ነሽ አሉ ሻደይ አሽከር አበባዬ . . . . . . . . .አሽከር አበባ / 2 / አሽከር ይሙት/2/ ይላሉ የኔታ አሽከር አይደለም ወይ የሚሆነው ጌታእያሉ ይጫወታሉ፡፡ እዚህ ላይ ሽከር የሚባለው ሎሌ ቅጥረኛ ስለሆነ ሰው አይደለም፡፡ ልጅ ለማለት ነው፡፡ በድሮው ጨዋታ ግን ከላይ ያየነው ግጥም የመጨራ ሁለት ግጥሞች እንዲህ ተብለው ይዜሙ ነበር፡-
አሽከር ይሙት/2/ ይላሉ የኔታ እርሶ አይሞቱም ወይ ያውም ዛሬ ማታየህ ግጥም በሁሉም የዋግ ምድር የተለመደ አይደለም፡፡ ወለህና ሐሙሲት አካባቢ ይህን ይጫወቱታል፡፡ ይህን ብለው የሚዘፍኑት አሽከር ይሙት ተብለው ተስድበው ሲለሚናደዱ ነው፡፡ ተሰዳቢዎቹ ግን የሃይል ምላሽ አይሰጡም፤ በባህሉ የሚፈቀድ ነውና፡፡ እንዲያዛ ከተጫወቱ በኋላ ስጦታ ይሰጣል፡፡ ገጠር ላይ እንደከተማው ገንዘብ አይደለም የሚሰጠው፡፡ እሚበላ የሚጠጣ ነበር የሚሰጠው፡፡ ያለው ከሆነ በእለቱ ይሰጣል፡፡ ማር ከሆነ ማር በጥብጦ ይሰጣል፤ እርጎ ካለው ደግሞ እርጎ ያቀርባሉ፡፡ በእድሜም በሃብትም የታወቁ ሰዎች ግን ብር ይሰጡ ነበር፡፡ ቀደን ሲል አንድ ብር አንኳ በጣም ብዙ ብር ነበር፡፡ በስተመዐረሻም እንዲህ ብለው ይዘፍናሉ፡- አስተሊለየ ለየ . . . . . . ስለል በየ /2/ እያሉ ይዘፍናሉ፡፡ ከዚያም ተመርቀው ወደሚቀጥለው ጨዋታ ይሄዳሉ፡፡ ሙሉ ስርዓቱ ይህን ይመስል ነበር፡፡ በማስከተል ደግሞ የድሮውና የአሁኑ ገጽታ እያስተያየን ያለውን ለውጥ እንመልከት፡