ቤተክርስቲያኑ የሚገኘው ከሰቆጣ ወደ ድሃና መውጫ መንገድ በአስር ኪ.ሜ በምዕራብ አካባቢ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኑ የተመሰረተው በዋግሹም ክንፌ በአስራ ስምንተኛው ዘመን ነው፡፡ በእውነቱ ቤተክርስቲያኑ ልዩ የሚያደርገው በከፍተኛ ሁኔታ ስዕሎቹ ባህሉን ጠብቆ መሳሉ እስካሁን ማራኪና ሳቢ የሆነ አስደናቂ ስዕሎች ይታያሉ ሰአሊ አቶ መረሳ ከሳላቸውም ጨርቆስ ስላሌ ቤተክርስቲያን በትግራይ ፡፡ በተጨማሪ ቤተክርስቲያኑ የድሮ ደውል ና አስደናቂ መስቀል በስጦታ ከዋግሹም ክንፌ የተሰጠ ይገኛል፡፡