ገዳሙ የሚገኘው ከሰቆጣ ወደ አበርገሌ መንገድ በሃምሳ ሁለት ኪ.ሜ በሰሜን በኩል ይገኛል በ1870 ዓ.ም ገዳም ሆነ፡፡ በንጉስ አፄ ሃይሌ ስላሴ 1961 ዓ.ም በልዩ ሁኔታ ታደሰ፡፡ ገዳሙም የበረሃ ገነት ብለው ይጠሩት የነበረ መሆኑን ጠቁመዋል ከአካባቢው አቀማመጥ ጋር ያመሳስለዋል ገዳሙ አረንጋዴና ክብ በሆነ ዛፎች የተከበበ ነው፡፡ በተጨማሪ መናኞች በመስኖ ግብርና ከጥቅምት እስከ ጥር ሙዝ፤ ሎሚና ሌሎችም በማምረት በረከቱን ለአካባቢው ያበረክታሉ ፡፡