ቤተክርስቲያኑ ከሰቆጣ ከተማ በሃመሳ አምስት ኪ.ሜ በምዕራብ አቅጣጫ ቦታ የሚገኝ በአፄ ካሌብ በስድተኛው ዘመን የተሰራ ነው፡፡ ይህ በእድሜ ትልቅ የድንጋይ ፍልፍል ቤተክርስቲያን ነው፡፡ አንዳንድ አስፈላጊ ቦታዎችን በድንጋይና በጭቃ ተሰርተዋል፡፡ አብዛኛው የድንጋይ ፍልፍል ከፍል ለበዓላት ነው፡፡ የሚገርመው የተፈጥሮ ድንጋይ ፍልፍል የተከማቸበት ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሃብት ነው፡፡ ባህላዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት መስጫ ጎጆ ከፊት ለፊቱ ይገኛል፡፡