ቤላ ተራራ

በሰሜኑ ኢትዮጵያ ከግርማ ሞጎሶች የታደለና የተቸሩት ተራሮች ውስጥ አንዱ የሆነው ቤላ ተራራ ነው፡፡ የተራራው መጠን ከባህር ጠለል 3700ሜትር በላይ ነው፡፡ ይህም የዋግ ኽምራ አስተዳደር ዞን ትልቁ ተራራ ነው እና የተለያዩ እንሰሳት መኖሪያና አትክልቶች፤ ወፎች፤ጅብና ሃገር በቀል ዛፎች እንደ ጥድና ወይራ ዛፍ መገኛ ነው፡፡ እንደጥቆማዎቹ ቤላ የተለያዩ መረጃዎች አሉት፡፡ ጥናቶች እንደሚሉት የተራራ ስም የተሰጠው ኤርትራዊ ተሰዳጆች ሰዎች ቢለን የሚባሉ ነበሩ ከብዙ አመታት ቡኃላ እነዚህ ሰዎች በታችኛው ቦታ የሚኖሩበት አካባቢ ነበር በዚህ ምክንያት መጠሪያው ከሰዎቹ ነገድ መጠሪያ ስም ሁኖ ቀረ ይባላል በሌላው ተከራካሪ ደግሞ መጠሪይ የተገኘው ጣሊያኖትች የሚያስደንቅና የሚማርክ እይታ ያለው በመሆኑ ተራራው ቤላ ብለው ጠሩት፡፡ ቤላ በጣሊንኛ ቆንጆ ቆንጆ ማለት ነው፡፡