ዋግ ኽምራ አንዷ የአማራ ክልል ልዩ ዞን ናት፡፡ ዋግ ኽምራን የሚዋስናት በምስራቅና በሰሜን ትግራይ፤ በደቡብ ሰሜን ወሎ በተለይ ላሊበላ እና በምዕራብ ደግሞ ጎንደር ናቸው፡፡ የዞኑ የቆዳ ስፋት 788,486 ኪ.ሜ2፤ ህዝብ ብዛት 418,817፤ ወንድ 211,403፤ ሴት 207,414 በ1999 ዓ.ም፡፡ ዕምነት በተመለከተ በይበልጥ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ 99.6%፤ 0.27% እስላም እና 0.13% ሌሎች የተለያየ እምነት ተከታይ ናቸው፡፡ በይፋ የሚነገረው ኽምጠኛ ነው፡፡ ኽምጠኛ የኩሽቲክ ቋንቋ ቤተሰብ ነው፡፡ የዞኑ አየር ንብረት 5.45% ደጋ፤ 31.43% ወይና ደጋና 63.42% ቆላ ነው፡፡ የብዙ ጨዎታ፤ ታሪክ፤ ባህልና ተፈጥሮ ባለሃብት እንዲሁም ደግ፤ ኩሩና እንግዳ ተቀባይ ህዝብ ነው፡፡
ዋግ ኽምራ ዛጉዌ ስረወ መንግስት መስራች ናት፡፡ የዞኑ ዋና ከተማ ሰቆጣ ናት፡፡ ሰቆጣ ከባህር ዳር 510 ኪ.ሜ፤ ከላሊበላ 128 ኪ.ሜ እና ከአዲስ አበባ 720 ኪ.ሜ ርቀት ትገኛለች፡፡ ለሰሜን ኢትዮጵያ ቅርብ ከተማ ናት፡፡ አያሌ መስህቦች አላት እነሱም የታሪክ ዋሻ፤ ነፃ ገበያ (ማክሰኞ) እንዲሁም በዞኑ ማራኪ ቦታዎችና በሰቆጣ ያልተነኩ ተፈጥሮ ሀብቶች አሉ ነገር ግን የማስተዋወቅና የገበያ ትስስር ትኩረት አልተሰጠም፡፡
አሁን የዞኑ ባህልና ቱሪዝም አቅሙን መጠቀም አለበት በተለይ የሚጎበኙ ቦታዎች ለጎብኚ በተሻለ ደረጃ መስራት አለበት፡፡