ተከዜ ግድብ በሰው ሰራሽ የተዘጋጀ ግድብ ለኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫነት የተሰራ ፕሮጀክት ነው፡፡ ባህሩ ላይ የሚገኙ በአለማችን ልዩ የሆኑ የምግብ አሳ መገኛው ብቸኛ ግድብ ነው፡፡ በአብርገሌ ወረዳ በኩል የአሳ ምርት በወጣቶች እየተሰራ የሚገኝ ነው እናም ባለሃብት ኢንቨስት አድርጎ በሰፊው የአሳ ምርትን መስራት የሚችልበት እድልም ሰፊ ነው፡፡ በተጨማሪም የመዝናኛና የሽርሽር ቦታ ለጎብኝዎች ማረፍያ አድርጎም መጠቀም የሚቻል ሰፊ መልካም ምድር አቀማመጥ ላይ ያለ ነው፡፡
ዋግ ኽምራ ዞን የከበሩ ማዕድናት መገኛ ስፍራ ናት፡፡ የተለያዩ የተፈጥሮ ማዕድናት አላት በተለይ የከበሩ ማዕድናት በብዛት የሚገኝ ነው፡፡
ሌላኛው ደግሞ የተፈጥሮ ማዕድን ብረት ነው፡፡ በአለማችን የመጀመሪያው 72.4 ፐርሰንት የሆነው ጠንካራው ብረት ማዕድን የሚገኘው በዚሁ ነው ስለዚህ ታላላቅ ኩባንያዎች በዚሁ ማዕድን ስራ ላይ በዋግ ኽምራ ተቋማቸውን ቢያሰማሩ ተመራጭ ነው፡፡