ከሰቆጣ እስከ ጭላ በምዕራብ አቅጣጫ በ45 ኪ.ሜ ርቀት አካበቢ ላይ የሚገኝ ቦታ ነው፡፡ ግራኝ በ14 ክፍለዘመን ከቤላ ተራራ በተቃራኒ ስፍራ የተቀመጠበት ነው፡፡ በታሪክ ጥንካሬውን ለማሳየት ሲል ትክል ድንጋይ አስቀመጠ ይህም አራት ማዕዘን የሆነ ቅርፅ ነው፡፡ በሌላኛው በኩልም ከጭላ አንደኛ ት/ቤት የመከላከያ ሰራዊትን የሚያሳይ መቀመጫ ቦታ አለ፡፡
የግራኝ ወታደር ክምር ድንጋይ
ሁለት የድንጋይ ክምር ሃውልት አሰቋቋመ፡፡ ያ ክምር የግራኝ ወታደርን ቁጥር የሚያሳይና ጥንካሬውንም ለክርስቲያኖች የሚያስፈራ ሰው ሃይል ነው፡፡ ጦርነቱ የእምነት አልነበረም ከክርስቲያኖች ስልጣናቸውን ለመውሰድና ንግዱንም ለመቆጣጠር የተደረገ ነበር፡፡